በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከነገ እለት ጀምሮ ይሰጣል፡፡
(ሰኔ 9/2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 10-12/2017 ዓ.ም ድረስ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በ5 የትምህርት ዓይነቶች በ192 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለ80,313 ተማሪዎች ፈተናው ይሰጣል።
በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች 2160 ፈታኝ ፤ 697 ሱፐር ቫይዘሮች 192 የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች ፈተናውን ለማስፈጸም የተመደቡ ሲሆን የሚሰጠው ፈተና ሰላማዊ ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ ከፈተና ህትመት ጀምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች የተጠናቀቁ በመሆናቸው ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም ፈተና እንዲሆን እንመኛለን፡፡
ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም ፈተና እንዲሆን እንመኛለን