Call us:
+912967565
|
Mail us for help:
info.haleluyapreprimaryandprimary.school@addislearning.edu.et
|
Help center
360° Support - We are here to assist you.
Haleluya Primary and Middle school
Haleluya Primary and Middle school
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
Announcement
Back
Announcement
News
Notice Board
Event
Promotion Form
Regional/National Result Submission Form
Online Admission
More
Resource
Publication
Policy&Strategy
Educational Statics
Legal Document
Gallery
Support
Submit Ticket
My Tickets
Service
About
Contact Us
Status
Login
Announcement
"በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን በኢ-ስኩል አጠቃቀም እና LAN SCHOOL ዙሪያ የልምድ ልዉዉጥ ተደረገ"
"በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን በኢ-ስኩል አጠቃቀም እና LAN SCHOOL ዙሪያ የልምድ ልዉዉጥ ተደረገ"
21st May, 2025
"በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን በኢ-ስኩል አጠቃቀም እና LAN SCHOOL ዙሪያ የልምድ ልዉዉጥ ተደረገ"
(ግንቦት 12/2017 ዓ.ም) በልምድ ልዉዉጡ መድረክ ሁሉም የመንግስት ቅድመ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ፣ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን፣ ሁሉም የክፍለ ከተማ ሱፐርቫይዘሮች፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አስተባባሪዎች፣ቡድን መሪዎች እና ባለሞያዎች፤የተሳተፉ ሲሆን በሁለት ርዕሰ ጉዳዮች ልምድ ልዉዉጥ ተደርጓል፡፡
አዲስ ከተማ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ሃሌሉያ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በአጠቃላይ ኢ-ስኩል ስራዎችን እና ስኩል ፖርታል አጠቃቀማቸዉን ያካፈሉ ሲሆን በአዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፀጋ ኃይሌ እና በሃሌሉያ ቅድመ አንደኛ ፣አንደኛ እና መካከለኛ ትምህርት ቤት በኩል አስቻለዉ ዘገዬ ስራቸዉን አቅርበዋል፡፡ በየካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ LAN SCHOOL አጠቃቀም ዙሪያ የአይሲቲ ላቦች ላይ ምልከታ በማድረግ ልምድ ልዉዉጥ የተደረገ ሲሆን የትምህርት ቤቱ የአይሲቲ ባለሙያዎች የላቦችን አደረጃጃት እና LAN SCHOOL ጠቀሜታ ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል፡፡
በመጨረሻም የአዲስ ከተማ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ዋና ር/መምህር አቶ እንዳልካቸዉ ደጀኔ፣ የሃሌሉያ ቅድመ እንኛ፣አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ዋና ር/ መምህር አቶ ግርማ ሽታ እና የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ በጋራ በልምድ ልዉዉጡ ተሳታፊዎች ለተነሱ ሃሳቦች ማጠቃለያ የሰጡ ሲሆን ተሳታፊዎችም የወሰዱትን ልምዶች እንደሚያሰፉ በመግባባት የዕለቱ ልምድ ልዉዉጥ ተጠናቋል፡፡
.