ለት/ቤቱ መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች በሙሉ
ከሰኔ 16 እስከ 20 /2017 ዓ.ም ድረስ በት/ቤታችን ለሚሰጠው የማጠቃለያ ፈተና ሙሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለ2017 የትምህርት ዘመን በወጣው መርሃግብር መሠረት ከሰኔ 16 እስከ 20 /2017 ዓ.ም ድረስ በት/ቤታችን ለሚሰጠው የማጠቃለያ ፈተና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ ሲሆን የትምህርት ቤቱ መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች በወጣው መርሃ ግብር መሠረት በመገኘት የሚናቸዉን እንድትወጡ እያሳወቅን ለተፈታኝ ተማሪዎችም መልካም ፈተና እንዲሆን እንመኛለን።
ት/ቤቱ